ዛሬ ምሽት 4፡00 ላይ ዲፖርቲቮ አላቬስ በሜዳው ሪያል ቫያዶሊድን ይገጥማል፡፡
በነገው ዕለት ደግሞ ምሽት 3፡ 45 ላይ ባርሴሎና በካምፕ ኑ ሪያል ሶሴዳድን ያስተናግዳል፡፡ የዲዬጎ ሲሞኔው አትሌቲኮ ዴ ማድሪድ ወደ ኤይባር ተጉዞ ጨዋታውን ያደርጋል፡፡
ሴልታ ቪጎ ከ ጂሮና እና ራዮ ቫዬካኖ ከሁሴካ በዕለቱ የሚደረጉ ሌሎች ግጥሚዎች ናቸው፡፡
የሳምንቱ ጨዋታዎች ዕሁድ ሲቀጥሉ ሪያል ማድሪድ በሳንቲያጎ ቤርናባው አትሌቲኮ ቢልባዎን ምሽት 12፡15 ሲል ያስተናግዳል፡፡
ሌቫንቴ ከኤስፓኞል፣ ሄታፌ ከሲቪያ፣ ቪያሪያል ከሌጋኜስ እና ሪያል ቤቲስ ከቫሌንሲያ ሌሎች ዕሁድ የሚከናወኑ ጨዋታዎች ናቸው፡፡
ላ ሊጋውን ባርሴሎና በ74 ነጥቦች እየመራ ይገኛል፡፡