Social

“ሃገሪቷ ያሏት ቅርሶች ብዛት ከእንክብካቤ እና እድሳት አቅም በላይ ነው” – ዶክተር ሂሩት ካሳው

በኢትዮጵያ ቅርሶችን ለመጠገን እና ለማደስ አስቸጋሪ የሆነው  ሃገሪቱ ያሏት ቅርሶች ብዛት ካላት የመንከባከብ  አቅም ጋር ስላልተመጣጠነ መሆኑን የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶ/ር ሂሩት ካሳው ተናገሩ።

ሚኒስትሯ ይህን ያሉት በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሚጠበቅበትን ሃላፊነት ለመወጣት ያደረገውን ጥረት እና የገጠሙትን ችግሮች በሚመለከት ለጋዜጠኞች መግለጫ በሰጡበት ወቅት ነው፡፡

ዶ/ር ሂሩት በመግለጫቸው በሀገራችን የቅርሶች ቁጥር እና ሀገሪቱ ያላት የገንዘብ እና የባለሙያ አቅም እንደማይመጣጠን ገልጸው ይህም ቅርሶችን ለመጠገን እና ለመጠበቅ እንዳዳገተ ተናግረዋል። ይህን ክፍተት ለማጥበብም በሚኒስቴሩ በኩል የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

የቱሪዝም መዳረሻ አስተዳደር፣አለም አቀፍ ቱሪዝም ፣የሀገር ውስጥ ቱሪዝም እና ፓርኮችን የማስተዳደር ስልጣን እና ሃላፊነትም  ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ  የተሰጡ ስልጣን እና ሃላፊነቶች መሆናቸውን በአዋጁ ያስቀምጣል።

ሚኒስትሯ እንደሚናገሩት ግን የሚኒስትር መስሪያቤቱ ተግባር እና ሃላፊነት አዋጁ ላይ ከተቀመጠበት  መንገድ ጋር ሲገናዘብ የመስሪያ ቤቱ ሃላፊነት ያልሆኑ ተጨማሪ ስራዎች የደራረበ  በመሆኑ በአፈፃፀም ላይ ክፍተት ፈጥሯል፡፡

 

በሚኒስትሯ መግለጫ ላይ ዜጎች ላይ የደረሰ መፈናቀል እና ቅርሶች ላይ የደረሱ ጉዳቶች በአመቱ የቱሪዝም ዘርፉን የጎዱ ምክንያቶች መሆናቸውም ተገልፃል፡፡

ሚኒስቴር መስሪያቤቱ ላይ የተደረገ አዲስ መዋቅር እና አደረጃጀት መስሪያቤቱን ወደስኬት የሚመራ ነው ብለዋል ሚኒስትሯ፡፡

በኢትዮጵያ የሆቴል ኮከብ ምደባ መጀመሩ እንደትልቅ ስኬት የሚታይ ነው ያሉት ሚኒስትሯ በአለምአቀፉ የንግድ ድርጅት ይሰጥ የነበረው የሆቴል ኮከብ ምደባ አሁን ሙሉበሙሉ በሀገራችን ባለሙያዎች መሰጠት መጀመሩ ጥቱ የውጭ ምንዛሬን ከማስቀረት እና የሀገር ውስጥ ባለሙያዎችን ለማፍራት ይረዳል ነው ያሉት፡፡

ባሳለፍነው ሳምንት የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር የ9 ወራት የስራ አፈፃፀም ለህዝብ ተወካዮች ምክርቤት ቀርቦ ከቅርስ እድሳት ጥበቃ እና ጥገና ጋር በተያያዘ ባለው የተጓደለ አፈጻጸም ከምክር ቤቱ አባላት ትችት እንደቀረበበት ይታወሳል፡፡

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami