SportSports

በህይወቴ ማንችስተር ዩናይትድን ለመጀመሪያ ጊዜ ልደግፍ ነው … ሚልነር

በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ተስተካካይ ጨዋታ በነገው ዕለት በማንቹሪያን ደርቢ ማንችስተር ዩናትድ እና ማንችስተር ሲቲ መካከል ኦልድ ትራፎርድ ላይ ይከናወናል፡፡

ይህ ጨዋታ ከሁለቱ ቡድኖች ባለፈ ለሻምፒዮንነት እየተፎካከረ ለሚገኘው ሊቨርፑል እና ሌሎች ታላላቅ ቡድኖች ትልቅ ትርጉም አለው፡፡

የቀያዮቹ ምክትል አምበል እና አማካይ ጄምስ ሚልነር ሰለጨዋታው አስተያቱን ሰጥቷል፡፡

ሚልነር ‹‹ በህይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ ማንችስተር ዩናይትድን ልደግፍ ነው ሲል ተናግሯል፡፡

‹‹ነገር ግን ጨዋታውን አልመለከተውም፤ ምክንያቱም ሀይልን ማዳከም ነው፣ ኳስን በሌላኛው ጎል ላይ እንድትቆጠር መማፀን ነው፡፡ ጨዋታውን እመለከተው እንደሆነ አላውቅም፣ ምናልባት ምግቦችን በመመገብ አሳልፍ ይሆናል›› ሲል ጨምሯል፡፡

ሊቨርፑል በ1989/99 የእንግሊዝ ሻምፒዮን ከሆነ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የሊጉን ዋንጫ ለማሳካት ዘንድሮ በ35 ጨዋታዎች ጉዞ 88 ነጥችን ሰብስበው ሊጉን ይመራሉ፤ የፔፕ ጓርዲዮላው ሲቲ ደግሞ በ34 ጨዋታዎች 86 ነጥቦችን ይዞ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡

ለቀያዮቹ መልካም ጉዞ ማድረግ ትልቅ ሚና ካለቸው ተጫዋቾች አንዱ የሆነው አንጋፋው እንግሊዛዊ ተጫዋች ጄምስ ሚልነር ደግሞ የማንችስተር ሲቲን ነጥብ መጣል እየሻተ የማይወደውን ዩናይትድ ድጋፍ ይሰጣል፡፡

ቀያዮቹ መቼም ቢሆን ለተቀናቃኞቻቸው ቀያይ ሰይጣኞች ፍቅር የላቸውም፤ ምክንያቱም ባላንጣነታቸው ገደብ የለሽ ነውና ፡፡ አሁን ግን የመርሲ ሳይዱ ሰዎች ለራሳቸው ጥቅም ሲሉ እየተናነቃቸውም ቢሆን ድል እና ሶስት ነጥብን ለማንችስተር ዩናይትድ ይማፀናሉ፡፡ የልመናቸው ዋና ምክንያት ደግሞ በሶስት አስርት ዓመታት ታሪካቸው ውስጥ የሚናፍቁት እና የሚሳሱለት የፕሪምየር ለጉን ዋንጫን ያስገኝላቸዋልና፡፡

የፔፕ ጓርዲዮላው ሲቲ ሽንፈት አሊያ የአቻ ውጤት የሚያስመዘግብ ከሆነ ሊቨርፑል ደግሞ በፋንታው ሁሉንም ቀሪ የሊግ ጨዋታዎች በድል የሚወጣ ከሆነ ዋንጫውን ወደ ካዝናው መቀላቀል ይችላል፡፡

ለዚህ ዋንጫ ሲባል ለአንድ ምሽት ሲባል ሊቨርፑላውያን ጠላታችን የሚሉትን ዩናይትድን ከክለቡ የልብ ደጋፊዎች አሰበልጠው ይደግፋሉ፡፡ ታዲያ ወደው ነው፡፡

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami