Uncategorized

አዲስ አበባ  ዘመናዊ ቤተ መፅሐፍት ለገነባላት ነው

አዲስ አበባ  ዘመናዊ ቤተ መፅሐፍት ለገነባላት ነው።

የቤተ-መፅሐፍት ግንባታው አራት ኪሎ ከፓርላማ ፊትለፊት ከአርበኞች ህንፃ ጎን የሚገነባ  ሲሆን በ38,687 ካሬ ሜትር ላይ ያርፋል ተብሏል፡፡

በአንድ ጊዜ 3ሺህ 500 ሰው የማስተናገድ አቅም ያለውና በቀን እስከ 10,000 ሰው መቀበል የሚችለው ማዕከሉ ለህፃናት እና አዋቂዎች የሚሆን  የማንበቢያ እና የአረንጓዴ ስፍራ አለው ነው የተባለው፡፡

እንደ ከንቲባ ፅህፈት ቤት ገለፃ  ከ100 ሰው በላይ የመያዝ አቅም ያላቸው ሶስት የስብሰባ አዳራሾች ያሉት ማዕከሉ   ለደራሲያን ፣ ከያኒያን እና የጥበብ ሰዎች የሚሆን የመለማመጃ እና የቴአትር ማዕከላት እንዲሁም ከ130 በላይ መኪኖችን የሚያቆም ዘመናዊ የመኪና ማቆሚያ ይኖሩታል፡፡

ይህ ለመዲናችን አዲስ አበባ ተጨማሪ ውበት የሚሰጥ እና በአይነትም ሆነ በይዘት ለሃገራችን የመጀመርያ የሆነው የአዲስ አበባ ቤተ-መፅሐፍት በሁለት ዓመት ውስጥ ወደ አገልግሎት እንደሚገባም ይጠበቃል፡፡

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami