PoliticsWorld News

ቻይና እና ቱርክ ከኢራን ጎን ነን ብለዋል፡፡

አሜሪካ ከኢራን ነዳጅ የሚገዙ ሀገራት በፈረንጆቹ ከግንቦት ወር ጀምሮ ግዣቸውን እነዲያቆሙ አስጠንቅቃለች፡፡

ቱርክ እና ቻይና ግን የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር የጣለው ማእቀብ ከወዳጃቸው ኢራን ነዳጅ ከማስገባት እንደማያግዳቸው ተናግረዋል፡፡

የኢራን ማእቀብ ለዓለም ገበያ የሚቀርበውን የነዳጅ ምርት ስለሚቀንሰው የዋጋ ማሻቀብ ይፈጥራል ለሚለው ስጋት ትራምፕ ከሳውዲ አረቢያ እና ከተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች ጋር መክረንበታል ሀሳብ አይግባችሁ እያሉ ነው፡፡

ህንድ እና ደቡብ ኮሪያም ነገሩን እያጤኑት እንደሆነ ፋይናንሺያል ታይምስ በዘገባው አስነብቧል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢራኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሞሀመድ ጃቫድ ዛሪፍ ሁሉን አሳታፊ የንግድ ፎረም ላይ ለመሳተፍ ወደ ኒው ዮርክ አቅንተዋል፡፡

 

መንገሻ ዓለሙ

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami