በደቡብ አፍሪካ በጎርፍ አደጋ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ50 በላይ ደርሷል፡፡
ኩዋዙሉ ናታን በተባለው የሀገሪቱ ምስራቃዊ ክፍል በሚገኝ አካባቢ የጣለው ከባድ ዝናብ ያስከተለው ጎርፍ መነዋሪዎች ላይትልቅ ጉዳት አድርሷል፡፡
አልጀዚራ እንደዘገበው የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች በቤቶች ፍርስራሾች ውስጥ የተቀበሩ ሰዎችን የማፈላለጉን ስራ እንደቀጠሉ ናቸው፡፡
በወደብ ከተማዋ ደርባን በርካታ ህንፃዎች እና መንገዶች በአደጋው ሳቢያ የፈራረሱ ሲሆን ኬፕ ታወን አካባቢ ሶስት ሰዎች መሞታቸውም ተሰምቷል፡፡
የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ አደጋው የደረሰበትን አካባቢ ከገጎበኙ በኋላ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ሰዎችን ለማዳን ለሚያደርጉት ጥረት ምስጋና አውርበዋል፡፡
መንገሻ ዓለሙ