Social

መንግሥት የሚደጉመው የፓልም ዘይት የጤናችግር  ስለሚያመጣ በሌሎች ፈሳሽ ዘይቶች እንዲቀየር ጤና ሚኒስቴር ጠየቀ

መንግሥት የሚደጉመው የፓልም ዘይት የጤናችግር  ስለሚያመጣ በሌሎች ፈሳሽ ዘይቶች እንዲቀየር ጤና ሚኒስቴር ጠየቀ።

ከፍተኛ የጤና ችግር ያመጣል የተባለው የፓልም ዘይት ከ90 እስከ 95 በመቶ በድጎማ የሚገባ ሲሆን፣ ይህንን ለመቀየር መጠየቁን ነው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ያስታወቀው፡፡

ሚኒስቴሩ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩትና የመድኃኒትና ምግብ ቁጥጥር ባለሥልጣን ያቀረባቸውን ጥናቶች ምክረ ሐሳብ መሠረት በማድረግ፣ የፓልም ዘይት በፈሳሽ ዘይቶች እንዲቀየር ለጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ ማሳወቁን ተናግሯል፡፡

ለንግድ ሚኒስቴር የተላከው ደብዳቤ እንደሚለው፣ ጤና ሚኒስቴር በገበያ ላይ ያሉ የምግብ ዘይቶች በጤና ላይ ችግር እየፈጠሩ ነው የሚል ምክረ ሐሳብ አቅርቧል፡፡

በአሁኑ ጊዜ እየቀረበ ያለው የፓልም ዘይት ለጤና ተመራጭ ስላልሆነ ደረጃ በደረጃ በሌሎች ለጤና ተስማሚና ተመጣጣኝ ዋጋ ባላቸው ፈሳሽ ዘይቶች (በሱፍ፣ በአኩሪ አተር፣ በሰሊጥ፣ በኑግና በሌሎች) እንዲተኩ ነው ሐሳብ የቀረበው፡፡

ሪፖርተር እንዳስነበበው ጤና ሚኒስቴር ይህን ችግር ለመቅረፍ የፓልም ዘይትን በሌሎች ፈሳሽ ዘይቶች መተካት አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሶ በጠየቀው መሠረት፣ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽሕፈት ቤት የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ንግድ ሚኒስቴር ጉዳዩን ገምግሞ የውሳኔ ሐሳብ ለጠቅላይ ሚኒስትር በጽሕፈት ቤት በአጭር ጊዜ እንዲያቀርብ ውሳኔ ተላልፏል፡፡

በዓለም አቀፍ ደረጃ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመሩ ሲሆን፣ በኢትዮጵያም ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ጫና ተላላፊ ከሆኑት ጋር እኩል የሰውን ጤና የሚገዳደሩ እየሆኑ መጥተዋል፡፡

ተላላፊ ላልሆኑ በሽታዎች ቀዳሚ መነሻ  የአመጋገብ ሥርዓትና የአኗኗር ዘይቤ ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥም የምግብ ዘይት አጠቃቀም ተጠቃሽ ነው፡፡

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami