Africa

አንድ የቦይንግ ምርት የሆነ አውሮፕላን በረራ ከጀመረ በኋላ በአውሮፕላኑ ጅራት ላይ እሳት መፍጠሩ ተሰማ

አንድ የቦይንግ ምርት የሆነ አውሮፕላን በረራ ከጀመረ በኋላ በአውሮፕላኑ ጅራት ላይ እሳት መፍጠሩ ተሰማ።

ባለቤትነቱ የኤር ዚምባብዌ  የሆነ ቦይንግ-ሰራሽ የቦይንግ 767-200ኤር አውሮፕላን ነው ሞተሩ በሚገኝበት የአውሮፕላኑ ጅራት ላይ  እሳት የፈጠረው፡፡
ይህ አውሮፕላን ከደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ አየር ማረፊያ  ከተነሳ በኋላ  ነው ብልሽቱ እና የእሳት ብልጭታው የታየው ሲል የሃገሪቱ አየር መንገድ ያስታወቀው፡፡

በብልሽቱ በረራው አለመስተጓጉሉና አውሮፕላኑ ሀራሬ በሰላም ደርሶ ማረፉን ኤር ዚምባብዌ ገልጿል፡፡

የዙምባቡዌ አየር መንገድ የብልሽቱን መንስኤ ለማወቅ ምርመራ እያካሄደ መሆኑን ገልጿል፡

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami