EthiopiaPolitics

የኢትዮጵያ የቱሪዝም መስህቦች በኩዌት እንዲተዋወቁ ተደረገ::

የኢትዮጵያ የቱሪዝም መስህቦች በኩዌት እንዲተዋወቁ ተደረገ::

ኩዌት የሚገኘው የኢፌዲሪ ኤምባሲ ከኢትዮጵያዊያን ኮሚዩኒቲ ጋር በመተባባር በኩዌት Yarmouk Cultura Center በተካሄደው የባህል ማስተዋወቂያ ሁነት ላይ በመሳተፍ የአገራችን የቱሪዝም መስህቦች የማሰተዋወቅ ሰራ ተሰርቷል።

በሁነቱ ላይ የኢትዮጵያን የተለያዩ ባህሎች፣ ታሪካዊ ቅርሶች፣ ባህላዊ አልባሳት፣ የቡና አፈላል ሥነ-ሥርዓትና የቱሪስት ሃብቶች በማስተዋወቅ የገጽታ ግንባታና የፕሮሞሽን ስራ ተከናውኗል።

የአገራችን ጥንታዊ የስልጣኔ መገለጫዎች፣ ታሪካዊ ቅርሶች፣ የመቻቻልና አብሮ የመኖር ዕሴቶች፣ ሀገራችን የመጀመሪያውን ሂጅራ ያስተናገደች ሀገር ስለመሆኗ በሁነቱ ለተገኙ ከ100 በላይ ተሳታፊዎች ገለጻም ተደርጓል።

በወቅቱ የቀረበው የኢትዮጵያ ባህላዊ የቡና አፈላል ሥነ-ሥርዓት የአብዛኛውን ታዳሚ ትኩረት የሳበ እንደነበረም ከታሳታፊዎች ከተገኘው መረጃ ማረጋገጥ ተችሏል።

አንድ ጣሪያ (One Roof) በሚል መሪ ቃል ሁነቱን በጋራ ያዘጋጁት Human Line Organization እና Social Work Society የተባሉ ድርጅቶች ሲሆኑ፤ በዚሁ ወቅት ኩዌት የሚገኘው ሐበሻ ባንድ የአገራችንን የተለያዩ የብሔር ብሔረሰቦች ባህላዊ ጭፈራዎች ማቅረቡን ከዉጭ ጉዳይ ቃላቀባይ ጽ/ቤት ያገኘነዉ መረጃ ያመለክታል፡፡

 

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami