AfricaPolitics

በሱዳን ያልታወቁ ጥቃት አድራሾች ስድስት ሰዎች ገደሉ፡፡

በሱዳን ያልታወቁ ጥቃት አድራሾች ስድስት ሰዎች ገደሉ፡፡

የሱዳን የሀኪሞች ማህበር በሰጠው መግለጫ አምስት ለተቃውሞ አደባባይ የወጡ ሰዎች እና አንድ ወታደራዊ ኦፊሰር መገደላቸውን ይፋ ድድጓርል፡፡

ሩሲያ ቱዳይ እንደዘገበው በማእከላዊ ካርቱም ድግያውን የፈፀሙት ግለሰቦች ማንነት ለጊዜው ባይታወቅም የፕሬዝዳንት ኦማር አልበሽር ታማኝ የነበሩ የደህንነት ሰዎች ሳይሆኑ እንደማይቀሩ ጥርጣሬ አለ፡፡

በነዚህ ባልታወቁ ግለሰቦች ህይዎታቸውን ካጡት ሰዎች በተጨማሪ 100 የሚሆኑ ሰወዎች የመቁሰል አደጋ እንደደረሰባቸውም ታውቋል፡፡

ጥቃት አድራሾቹ በሱዳን መከላከያ ዋና መስሪያ ቤት አቅራቢያ በተሰበሰቡት ተቃዋሚዎች ላይ የፈፀሙትን ግድያ የሱዳን ወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤት ሃላፊ ጄኔራል አብደል ፈታህ ቡርሀን በፅኑ አውግዘውታል፡፡

አደጋው የደረሰው ወታደራዊ ምክር በቤቱ እና ተቃዋሚ ፓርቲዎች የሽግግር ጊዜ አመራሮች ውክልና እና አደረጃጀት ላይ ስምምነት ደርሰናል ባሉበት ወቅት መሆኑ ያለውን ተስፋ እንዳያደበዝዘው ተሰግቷል፡፡

መንገሻ ዓለሙ

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami