EthiopiaSportSports

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ25ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ እና በቀጣዮቹ ቀናት ይደረጋሉ፡፡

የሳምንቱ መርሀግብር ጨዋታዎች ዛሬ ቀን 9፡00 ሰዓት ደደቢት እና ባህር ዳር ከነማ ትግራይ ላይ በዝግ ስታዲየም በሚያደርጉት ጨዋታ ይጀመራል፡፡

በነገው ዕለት ሁለት ጨዋታዎች ሲደረጉ፤ ወላይታ ድቻ ወደ ትግራይ አቅንቶ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲን 9፡00 ላይ ይጎበኛል፡፡

በአዲስ አበባ ስታዲየም 10፡00 ላይ ደግሞ መከላከያ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ይገናኛሉ፡፡ ጊዮርጊስ አሰልጣኝ ስቱዋርት ሃልን ካሰናበተ በኋላ በምክትሉ ዘሪሁን ሸንገታ እየተመራ የመጀመሪያ ግጥሚያውን ይጎበኛል፡፡

ዕሁድ ደግሞ አራት ግጥሚያዎች በክልል ስታዲየሞች በተመሳሳይ 9፡00 ላይ ሲከናወኑ፤ በ48 ነጥቦች የሊጉ አናት ላይ የተቀመጠው መቐለ 70 እንደርታ በትግራይ ስታዲየም ሀዋሳ ከተማን ያስተናግዳል፡፡

መቐለን በሁለት ነጥብ አንሶ የሚከተለው የጎንደሩ ፋሲል ከነማ ደግሞ በአፄ ፋሲለደስ ስታዲየም ከጅማ አባ ጅፋር ጋር ይጫወታል፡፡

አዳማ ከተማ ወደ ምስራቅ ኢትዮጵያ አምርቶ ከድሬዳዋ ከነማ ጋር ይፋለማል፡፡

ወራጅ ቀጠና ውስጥ የሚገኙት ደቡብ ፖሊስ እና ስሑል ሽረ ሀዋሳ ላይ ይጫወታሉ፡፡

የሳምንቱ መርሀግብር የመዝጊያ ግጥሚያ በኢትዮጵያ ቡና እና ሲዳማ ቡና መካከል በአዲስ አበባ ስታዲየም 10፡00 ላይ ይከናወናል፡፡

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami