በሚቀጥለው የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የውድድር ዓመት የሚሳተፍ ሶስተኛውን ክለብ ለመለየት ዛሬ አመሻሽ 11፡00 ሰዓት በግዙፉ ዌምብሌይ ስታዲየም ይደረጋል፡፡
ተፋላሚዎቹ ደግሞ አስቶን ቪላ እና ደርቢ ካውንቲ ናቸው፤ በቼልሲ አብረው ስኬትን የተቋደሱት ጆን ቴሪ እና ፍራንክ ላምፓርድ ደግሞ በአሰልጣኝነት የተለያዩ ቡድኖችን ይዘው ተፋጥጠዋል፡፡
የቪላ አሰልጣኝ ዲን ስሚዝ ምክትል ሆኖ እያገገለገለ የሚገኘው ቴሪ ሲሆን ላምፓርድ ደርቢን በዋና አሰልጣኝነት በተረከበበት ዓመት ወደ ሊጉ ሊያሻግረው ጫፍ ላይ ደርሷል፡፡
በደርሶ መልስ ጨዋታዎች አስቶን ቪላ ዌስት ብሮም አልቢዮንን እንዲሁም ደርቢ ካውንቲ የማርሴሎ ቤልሳውን ሊድስ ዩናይትድ በመጣል ነበር ለዚህ የፍፃሜ ጨዋታ መብቃት የቻሉት፡፡
የጨዋታው አሸናፊ ከኖርዊች እና ሼፊልድ ዩናይትድ በመከተል፤ 170 ሚሊዬን ፓውንድ ጋር ሶስተኛው 2019/20 የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ተሳታፊ ቡድን መሆኑን ያረጋግጣል፡፡
በቻምፒዮንሽፑ የውድድር ዓመት ቪላ በፍራንክ ላምፓርድ ቡድን ላይ ሁለቱን ጨዋታ (በ3 ለ 0 እና 4 ለ 0) ድል በማድረግ የበላይነት አለው፡፡