የባህርዳር ጤና ጣቢያ የቤት ለቤት ተመላላሽ ህክምና መስጠት መጀመሩ ተገለፀ፡፡
ጤና ጣቢያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሞደልነት ተመርጦ ለነዋሪዎቹ የቤት ለቤት ህክምና መስጠት መጀመሩን የጤና ጣቢያው ጊዜያዊ ተወካይ አቶ ተመስገን ደሌ ገልጸዋል፡፡
በስሩ ካሉት አራት ቀበሌዎች በተጨማሪ ለአጎራባችና ከገጠር ቀበሌ ለሚመጡትም አገልጋይ እንደሆነ የጤና ሚኒስቴር አስነብቧል፡፡
ጤና ጣቢያው በእናቶችና ህፃናት ጤና፣ተላላፊ የሆኑና ያልሆኑ በሽታዎችን በመከላከልና ወቅት ጠብቀው የሚከሰቱ እንደ ወባ እና አተት የመሳሰሉ በሽታዎችን ቀድሞ በመቆጣጠር በኩል የቤት ለቤት ህክምናው ጠንካራ አቅም እየሆነ ነው ብለዋል።