የፊቼ ጫምባላላ በዓል በሀዋሳ ከተማ እየተከበረ ነው
የሲዳማ ብሄር ዘመን መለወጫ ፊቼ ጫምባላላ በዓል በሀዋሳ ከተማ እየተከበረ ነው።
ዛሬና የጀመረዉ የሲዳማ ብሄር ዘመን መለወጫ ፊቼ ጫምባላላ በሀዋሳ ከተማ በደማቅ ሁኔታ እየተከበረ ይገኛል።
የፊቼ ጫምባላላ በዓል እየተከበረ የሚገኘውም በዓሉን በሚያንፀባርቁ የተለያዩ ባህላዊ ስነስረዓቶች ነው።
ዛሬ በሀዋሳ በሚከናወነው የፊቼ ጫምባላላ በዓል ስነ ስርዓት ላይ የሲዳማ ብሄር ባህልና ቋንቋ የተመለከተ ሲምፖዚዬም ይካሄዳል።
የሲዳማ ሕዝብ የዘመን መለወጫ በዓል ፊቼ ጫምባላላ በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) አለም አቀፍ ቅርስ ሆኖ መመዝገቡ የሚታወቅ ነው።
በዓሉ ነገም ተከብሮ ይዉላል፡፡