EconomyEthiopia

ኢትዮጵያ ባለፉት አስር ወራት ከዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት እና መንግስታት የ4.7 ቢሊዮን ዶላር የልማት ድጋፍ እንዳገኘች የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ኢትዮጵያ ባለፉት አስር ወራት ከዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት እና መንግስታት የ4.7 ቢሊዮን ዶላር የልማት ድጋፍ እንዳገኘች የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ  በህዝብ ተወካች ምክር ቤት ቀርበዉ የሚኒስቴሩን የአስር ወራት አፈጻጸም ሪፖረት ባቀረቡበት ወቅት እንደተናገሩት፤ ሀገሪቱ ከዓለም አቀፍ ፋይናንስ ተቋማትና ከተለያዩ መንግስታት በብድርና እርዳታ 5.7 ቢሊየን ዶላር ለማግኘት አቅዳ በአስር ወራት ዉስጥ ግን የ4.7ቢሊዩን ዶላር ድጋፍ እንዳገኘች ተናግረዋል፡፡

በበጀት አመቱ ላይ መንግስት የተረጋጋ የማክሮ ኢኮኖሚ እንዲኖር ጥብቅ የፊሲካል ፖሊሲ ተግባራዊ ማደረጉን እና የመንግሥት ወጪ በገቢው እንዲሸፈን ተደረጓል፡፡

ሀገሪቱ ከወጪ ንግድ 2.1 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቷን የተጠቀሰ ሲሆን፤ከ2010 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ከተገኘው ገቢ ሲነጻጸር በ187.1 ሚሊዮን ዶላር ቅናሽ አሳይቶል፡፡

እንደ ገንዘብ ሚነስቴር ገለፃ በ10 ወራት ዉስጥ 174 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር አጠቃላይ የፌዴራል መንግስት የተጣራ ገቢ የተሰበሰበ ሲሆን 251 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር ደግሞ ወጪ መሆኑ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

አገሪቱ ከገጠማት የውጭ ምንዛሪ እጥረት አኳያ የውጭ ዕዳ ክፍያ ጫና ለማቃለል እና በቀጣይ ዕዳ የመክፈል አቅምን ለማጠናከር ከቻይና የፋይናንስ ተቋማት ጋር ድርድሮችን በማድረግ የወለድ መጠን ቅነሳ፣ የእፎይታ እና የመክፈያ ጊዜ እንዲራዘም ተደረጓል፡፡

 

 

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami