የሱዳን ተቃዋሚዎች በመጭው እሁድ ለታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ ቀጠሮ ይዘዋል፡፡
እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ሰኔ 3 ካርቱም ላይ በወታደራዊ ሀይሉ የተበተኑት ሱዳናዊያን አሁንም ስልጣን ለሲቪል አስተዳደር ካልተሰጠ በተቃውሟቸው እንደሚገፉበት ተናግረዋል፡፡
አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደዘገበው ተቃዋሚዎቹ ለሳምንታት ከቆዩበት ጎዳና በፀጥታ ሀይሎች ሲባረሩ ደረሰብን የሚሉት ዓይነት ጉዳት ዳግም ሊደርስባች እንደሚችል ስጋት አለብን ብለዋል፡፡
የአፍሪካ ህብረት የሱዳን ወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤት ስልጣኑን አብላጫ ቁጥር ላለው የሲቪል ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲያስረክብ አዲስ ሀሳብ አቅርቧል፡፡
ተቃዋሚዎቹ የወታደራዊ ምክር ቤቱ የፀጥታ ሀይሎች 130 ሰዎችን ገድለውብናል ሲሉ ምክር ቤቱ በበኩሉ የሟቾች ቁጥር ከ61 አይበልጥም ማለቱ ይታወሳል፡፡
መንገሻ ዓለሙ