ኬንያ በሙስና የጠረጠረቻቸውን ባለ ስልጣኖቿን አሰረች፡፡
አቃቤ ህግ ፖሊስ ይዞ እንዲያቀርብለት ተጠርጣሪዎችን በስም ጠቅሶ መግለጫ መስጠቱን ተከትሎ የኬንያ የፋይናንስ ሚኒስትር እና የሀገሪቱ የአካባቢ ጥበቃ ሃላፊ እጃቸውን በፈቃዳቸው ሰጥተዋል ነው የተባለው፡፡
አልጀዚራ እንደዘገበው ኬንያ በሙስና ወንጀል ተሳትፈዋል ያለቻቸውን 28 ባለ ስልጣኖቿን በቁጥጥር ስር አውላቸዋለች፡፡
የኬንያ ፖሊስ ሀላፊ ጆርጅ ኪንቶቲ ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደተናገሩት ከሆነ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉት ተጠርጣቂዎች በማረፊያ ቤት ሆነው ፍርድ ቤት የሚቀርቡበትን ጊዜ እየተጠባበቁ ነው፡፡
ኬንያ በታሪኳ በስልጣን ላይ ያሉ ሚስትሮቿን ስታስር የፋይናንስ ሚኒስትሩ ሄንሪ ሮቲች የመጀመሪያው ናቸው ተብሏል፡፡
አቃቤ ህግ በሰጠው መግለጫ ሮቲች እና ተባባሪዎቻቸው በፈፀሟቸው ኢኮኖሚያዊ አሻጥሮች እስከ ስምንት የሚደርሱ ክሶች ይጠብቋቸዋል ብለዋል፡፡
መንገሻ ዓለሙ