የደቡባዊ አፍሪካ የልማት ማህበረሰብ /ሳድክ/ ዚምባቡዌ ማእቀብ እንዲነሳላት ጥሪ አቀረበ፡፡
በደቡባዊ አፍሪካ ሀገራት የተቋቋመው እና 16 ሀገራት በአባልነት የተካተቱበት ሳድክ የአውሮፓ ህብረት እና አሜሪካ በዚምባቡዌ ላይ የጣሉት ማእቀብ በአስቸኳ እንዲነሳ ጠይቋል፡፡
የወቅቱ የሳድክ ሊቀመንበር የሆኑት የታንዛኒያው ፕሬዝዳንት ጆን ማጉፉሊ ባስተላለፉት መልእክት ዚምባቡየን በማእቀብ ሳቢያ የገጠማት ችግር ለቀጠናው ሀገራትም የሚተርፍ በመሆኑ ሊታሰብበት ይገባል ብለዋል፡፡
ዚምብቡዌ አሁን በአዲስ የአስተዳደር ዘይቤ ውስጥ እንደሆነች እና ወደፊት ለመራመድ ዝግጁ መሆኗን ከግምት ውስጥ በማስገባት ምእራባዊያን የጣሉባትን ማእቀብ ሊያነሱላት ይገባልም ብለዋል ሊቀመንበሩ፡፡
ፕሬዝዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ በበኩላቸው ማእቀቡ የገሪቱን ልማት በእጅጉ እንዳዳከመው በመጥቀስ ይህን ያደረጉ ሀገራትን ወቅሰዋል፡፡
በዚምብቡዌ በአሁኑ ወቅት በተከሰተው የዋጋ ግሽበት ሳቢያ የነዳጅ፣ የሀይል እና የመሰረታዊ ሸቀጦች ዋጋ በማሻቀቡ ህዝቡ መበመንግስት ላይ ከፍተኛ ተቃውሞ እያነሳ ነው፡፡
አሜሪካ ብቻ 141 የበዚምባቡዌ ተቋማት እና ባለ ስልጣናት ላይ ማእቀብ መጣሏ እና ባለፈው መጋቢት ይህንኑ ማእቀብ ለአንድ ዓመት እንዲራዘም ፕሬዝዳንት ዶናልድ ተራምፕ መወሰናቸው ይታወሳል፡፡
መንገሻ ዓለሙ