DisasterEthiopia

በሰሜን ጎንደር ደጋማ ወረዳዎች የበረሃ አንበጣ መንጋ እየተስፋፋ መሆኑ ተገለጸ፡፡

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3፣ 2012 በሰሜን ጎንደር ዞን ደጋማ ወረዳዎች ማለትም በየዳ፣ ጠለምትና ጃናሞራ ወረዳዎች ባለፈ አድማሱን በማስፋት በወረዳዎች ስር በሚገኙ 32 ቀበሌዎች ላይ የአንበጣ መንጋው ተስፋፍቷል ተብሏል።

የሰሜን ጎንደር ዞነ ግብርና መምሪያ የኤክስቴንሽን ቡድን መሪ አቶ ዋለ መርሻ ለአማራ ብዙሃን መገናኛ እንደገለጹት፡ መንጋው አሁን ላይ የሰብል ወቅት ባለመሆኑ ጉዳት ባያደርስም የመስኖ ሰብሎች ለይ ጥፋት እንዳያደርስ ጥረት እየተደረገ መሆኑንም አስታውቀዋል።

በተጨማሪም  ኅብረተሰቡ የሰብል ወቅት ባለመሆኑን  አንበጣዉን ለመከላከል ቸልተኝነት ማሳየቱን ያመላከቱት ባለሙያው፡ የበረሃ አንበጣ መንጋው ተመቻችቶ ከተቀመጠ እንቁላል ሊጥል ስለሚችል ለኅብረተሰቡ የግንዛቤ ፈጠራ ሥራ እየተሠራ መሆኑንም ገልጸዋል።

በባህላዊ ዘዴ መንጋውን ለመከላከል ጥረት እየተደረገ ቢሆንም ፤ ወደ ተራራማ አካባቢ ሲንቀሳቀስ በባህላዊ ዘዴ መከላከሉን አስቸጋሪ እንደሆነ ተገልጿል።

የበረሃ አንበጣ በቆላማ አካባቢዎች እንደሚከሰት ቢታወቅም በሰሜን ጎንደር የተከሰተባቸው ሦስቱ ወረዳዎች በአብዛኛው ደጋማ ናቸው፡፡

ከዚህ ቀደም በደቡብና ሰሜን ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ፣ ምዕራብና ምሥራቅ ጎጃም ዞኖችና ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር መከሰቱ ይታወሳል፡፡

Tags
Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami