አገር አቀፍ የተቀናጀ የትራንስፖርት ማስተር ፕላን ፕሮጀክት በይፋ ተጀመረ
አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 30 ፣ 2012 የትራንስፖርት ሚኒስቴር እንዳስታወቀዉ አገር አቀፍ የተቀናጀ የትራንስፖርት ማስተር ፕላን ፕሮጀክትን ለማስጀመር በተደረገው የቪዲዮ ኮንፈረንስ ወይይት ላይ የትራንስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ ፕሮጀክቱ በታቀደለት ግዜና ጥራት እንዲጠናቀቅ ሁሉም ባለድረሻ አካላት አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ ጠይቀዋል፡፡ሚኒስትሯ አለም አቀፍና አገር አቀፍ ወቅታዊ ሁኔታን ከግምት በማስገባት ስራው በታቀደለት ግዜ ለመፈጸም የሚስችል ልዩ የአስራር ስርዓት መዘርጋቱንም ገልፀዋል፡፡የትራንስፖርት ማስተር ፕላን ፕሮጀክቱ ከአፍሪካ ልማት ባንክ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ እና በሁለት አለም አቀፍ አማካሪ ድረጅቶች ጋር የሚከናወን ነው፡፡ፕሮጀክቱ ለ20 አመት የሚያገለግል ሲሆን በአገሪቱ የትራንስፖርት ፍሰቱን በማሳለጥ ለኢኮኖሚው እድገት የሚኖረውን ድረሻ ያሳድጋል ተብሎ ይጠበቃል።