HealthPolitics

ደቡብ ኮሪያ ከኮሮና ቫይረስ ጋር እየታገለች ባካሄደችው ምርጫ የገዥው ፓርቲ ማሸነፉ ይፋ ሆነ፡፡

ደቡብ ኮሪያ ከኮሮና ቫይረስ ጋር እየታገለች ባካሄደችው ምርጫ የገዥው ፓርቲ ማሸነፉ ይፋ ሆነ፡፡ሰዎች በቤት ውስጥ እንዲቀመዩ በሚመከርበት እና ሀገራ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እየደነገጉ ባሉበት ወቅት ደቡብ ኮሪያ ሀገራዊ ምርጫዋን በስኬት ማጠናቀቋን ተናግራለች፡፡የሀገሪቱ ባለ ስልጣናት ለምጫ አደባባይ ወጡ ሰዎች ርቀታቸውን ጠብቀው እንዲሰለፉ እና ራሳቸውን እንዲጠበወቁ ልዩ ጥንቃቄ አድርገን ነበር ብለዋል፡፡ቢቢሲ እንደዘገበው ፕሬዚዳንት ሙን ጃይ ኢን የሚመሪት ዲሞክራቲክ ፓርቲ ካት 300 መቀመጫዎች ውስጥ 163ቱ አሸንፏል፡፡የገዥው ፓርቲ አጋር የሆነው ፕላትፎርም ፓርቲ 17 መቀመጫዎችን የማሸነፉ ዜና እየተሰማ በመሆኑ መንግስት በጠቅላላው ወደ 180 ድምፅ በማግኘት አስተማማኝ ድል ማስመዝገቡ ነው የተነገረው፡፡

በኮሮና ቫይረስ ስጋት ምክንያት የመራጮች ቁጥር ይቀንሳል ተብሎ ተፈርቶ የነበረ ቢሆንም የአሁኑ ምርጫ በ18 ዓመት ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ መራጭ ተመዝግቦበታል ተብሏል፡፡ደቡብ ኮሪያ በአሁኑ ጊዜ ወደ 60 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች በለይቶ ማቆያ ስፍራ ያሏት ሲሆን ከ10 ሺህ በላይ ዜጎቿ በቫይረሱ ተይዘዋል፤ከነዚህም መካከል ከ200 በላይ የሚሆኑት ሞተዋል፡፡

Tags
Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami