COVID-19HealthNewsኢትዮጵያ

በኢትዮጵያ ከኮሮና ቫይረስ ያገገሙ  ሰዎች ቁጥር  25 ደረሰ፡፡

በኢትዮጵያ ከኮሮና ቫይረስ ያገገሙ  ሰዎች ቁጥር  25 ደረሰ፡፡የጤና ሚኒስቴር እንዳስታወቀዉ ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ የላቦራቶሪ ምርመራ  9 መቶ 33 ሰዎች ተመርምረዉ  በ1 ሰዉ ላይ ቫይረሱ ተገኝቷል፡፡ቫይረሱ የተገኘባቸዉ የ60 ዓመት ሴት ሲሆኑ ከእንግሊዝ የመጡና በአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ዉስጥ የነበሩ ናቸዉ፡፡በ24 ሰዓት ዉስጥ 4 ሰዎች ያገገሙ ሲሆን ሁለቱ ከአዲስ አበባና ሁለቱ ከባህርዳር ናቸዉ፡፡ባጠቃለይ በለይቶ ማቆያ ህክምና ዉስጥ የሚገኙት 87 ሰዎች ናቸዉ፡፡በአጠቃላይ  በኢትዮጵያ 11 ሺህ 6 መቶ 69 ሰዎች ተመርምረዉ 1መቶ 17 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፡፡

የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ እንዳስታወቁት በሁለት ቀናት ዉስጥ ምርመራ ከተደረገላቸዉ 1 ሺህ 8 መቶ 98 ሰዎች መካከል የኮሮና ቫይረስ የተገኘበት አንድ ግለስብ ብቻ መሆኑ የበሽታዉን ስርጭት መቀነሱንም ሆነ በሕብረተሰቡ ዉስጥ የበሽታዉ ስርጭት አለመኖሩን የሚገልጽ እንዳልሆነ መረዳት እንደሚስፈልግ አሳስበዋል፡፡አስካሁንም   ድረስ ምርመራ የተደረገላቸዉና ቫይረሱ እንዳለባቸዉ የተገለጸዉ በአብዛኛዉ በአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ የነበሩና የተወሰኑት ደግሞ ቫይረሱ እንዳለባቸዉ ከታወቁ ሰዎች ጋር የቅርብ ንኪኪ የነበራቸዉ ሰዎች መሆናቸዉ ተገልጿል፡፡

Tags
Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami