አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 16 ፣ 2012 ማንኛዉም ሰዉ ደም ለመለገስ ሲመጣ ፕሮግራም አሲዞ እንዲመጣ የሚያደርግ መተግበሪያ እየተዘጋጀ መሆኑን የቢሄራዊ ደም ባንክ አስታወቀ፡፡የደም ባንኩ ኮሮና ቫይረስ በኢትዮጵያ ከተከሰተ የመጀመሪያዎቹ ሳምንታት ላይ የደም እጥረት ነበረ አሁን ላይ ግን በተሰራዉ የግንዛቤ ማስጨበጫ ታላቅ መነቃቃት መታየቱን ያስታወቀ ሲሆን የረመዳንን ፆም ምክንያት በማድረግ ሁሉም የብሄራዊ ደም ባንክ ቅርጫፎች እስከ ምሽቱ 4 ሰዓት እንዲሰሩ መደረጉን የደም ባንኩ ከአርትስ ቲቪ ጋር በነበረዉ ቆይታ አብስሯል፡፡በተጨማሪም መተግበሪያዉ ኮሮና ቫይረስን ለመከላከል በሚደረገዉ ጥረት ላይ እክል የሆነዉን ሰዎችን በጋራ የመሰባሰብ ሂደት ያስቀራል ነዉ የተባለዉ፡፡
በሰላማዊት ደበበ