አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 21 ፣ 2012 በማሊ የሥደተኞች ጣቢያ በእሳት በመውደሙ ዜጎች ለሁለተኛ ስደት ተጋልጠዋል::
በማሊ በተከሰተው የርስበበርስ ግጭት ምክንያት መኖሪያ ቀያቸውን ለቀው በጊዜያዊ መጠለያ የነበሩ ሰዎች መኖሪያቸው ሙሉ በሙሉ መውደሙ ተሰምቷል፡፡አሶሼትድ ፕሬስ እንደዘገበው በዚህ ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያ ውስጥ እስከ ሁለት ዓመት የቆዩ ከ1 ሺህ በላይ የሚሆኑ ማሊያዊያን ስደተኞች ይኖሩ ነበር፡፡
ስደተኞቹ እንደተናገሩት አለን የሚሉት ንብረት ሁሉ በሙሉ በእሳቱ ወድሞባቸዋል ነው የተባለው፡፡የሀገሪቱ ባለስልጣናት በበኩላቸው ለሁለተኛ ጊዜ ለስደት የተዳረጉትን ዜጎች ቦታ ፈልገው በአስቸኳይ እንደሚያሰፍራቸው ቃል ገብተውላቸዋል፡፡ማሊ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣር ከ2012 ጀምሮ በድንገት ጥቃት እየፈፀሙ የብዙ ንፁሀን ዜጎችን ህይዎት ከሚቀጥፉ እና ለሰቆቃ እየዳረጉ የሚገኙ አክራሪ ሚሊሻዎችን ለማጥፋት እየታገለች ትገኛለች፡፡በድንገት ለአደጋ የተጋለጡት እነዚህ ስደተኞች ተረጋግተው መኖር እስከሚጀምሩ በመተፋፈግ ስለሚቆዩ ለኮሮና ቫይረስ የመጋለጥ እድላቸው ከፍተኛ በመሆኑ መንግስት ስጋት ገብቶታል ተብሏል፡፡