አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 23፣ 2012 በወላይታ ዞን የአዋጁን ድንጋጌ ተላልፈዋል የተባሉ 700 አሽከርካሪዎች ተቀጡበወላይታ ዞን የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የክልከላ ድንጋጌን ተላልፈው ተገኝተዋል የተባሉ 700 አሽከርካሪዎች መቀጣታቸውን የዞኑ የኮሮና መከላከል ግብረ ኃይል ገለጿል፡፡በሌላ በኩል በሃዲያ ዞን የሆሳዕና ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ኮሮናን ለመከላከል የሚረዱ ከእጅ ንክኪ ነፃ የሆኑ የእጅ መታጠቢያዎችን በፈጠራ ስራ በማውጣት ለዞኑ አስተዳደር አስረክቧል።
በወላይታ ዞን የግብረ ኃይሉ አባልና የመንገድና ትራንስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ፎላ እንደገለጹት አሽከርካሪዎቹ የተቀጡት በአዋጁ ድንጋጌ መሰረት 50 በመቶ የጭነት ልክ ተላልፈው በመገኘታቸው ነው።ተላለፈው የተገኙት 700 አሽከርካሪዎች መሆናቸውን አመልክተው በዚህም ከ330 ሺህ ብር በላይ እንዲቀጡ መደረጉን አስታውቀዋል።መንገድ ደህንነት ተቆጣጣሪዎች ደንብ በሚጥሱ አካላት ላይ እርምጃ የመውሰድ ተግባራቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉም አሳስበዋል።