COVID-19HealthNewsWorld News

አንቶኒዮ ጉቴሬዝ የዓም መሪዎች መናበብ ባለመቻላቸው ህዝባቸውን ከኮቪ 19 መታደግ አቅቷቸዋል አሉ::

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 23፣ 2012 የተባበሩት መንግስታ ድርጅት ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ከቢቢ ጋር ባደረጉት ቀለ መጠይቅ መላው ዓለም በአንድነት ቢተባበር በሽታውን መግታት ይቻል ነበር ብለዋል፡፡የሀገራት መሪዎች እርስበርስ ተግባብተው እና አንድ ሆነው ከመስራት ይልቅ አንዱ በሌላው ላይ ጣት በመጠቋቆም በየራሳቸው መንገድ መጓዛቸው ጎድቷቸዋል ነው ያሉት ዋና ፀሀፊው፡፡ሁኔታው በጣም እንዳሳሰባቸው የገለፁት ጉቴሬዝ አሁንም ቢሆን አልረፈደም ተባብሮ ቫይረሱን ለማጥፋት ከታሰበ ጊዜ አለ ብለዋል፡፡

ከአሁን ቀደም በተደጋጋሚ የሚሰጡ መግለጫዎች እና የማስጠነንቀቂያ መልዕክቶች ወደ ጎን መባላቸው ዓለም ብዙ ዋጋ መክፈሏንም ተናግረዋል፡፡አሜሪካ ለዓለም ጤና ድርጅት የምታዋጣውን ገንዘብ በከልከሏ ስህተት ነው ብለው ያምናሉ ወይ ተብለው ሲጠየቁም ተቋሙን መደገፍ ለታዳጊ ሀገራት በጣም ወሳኝ ነው፣ ይህን ማድረግ ደግሞ የለጋስነት ምከልክት ሳይሆን ለራስ ከማሰብ የሚመነጭ ነው ብለዋል፡፡ምክንያታቸውን ሲያብራሩም በሽታው በአንዱ የዓለም ክፍል ቢጠፋ በሌላው ክፍል ከተስፋፋ ተመልሱ ሁሉንም ማዳረሱ አይቀርም፤ እናም በኢኮኖሚ ደከም ያሉትን መደገፍ ለራስም ጭምር ማሰብ ነው ሲሉ አሳስበዋል፡፡

Tags
Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami