አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 28፣ 2012 ናይጄሪያ የእንቅስቃሴ እገዳ ባነሳች በሰዓታት ውስጥ የታማሚዎች ቁጥር በ245 መጨመሩ ድንጋጤን ፈጥሮባታል::የሀገሪቱ የበሽታዎች መቆጣጠሪያ ማዕከል እንዳለው በናይጄሪያ ከአሁን በፊት በአንድ ቀን ውስጥ ይሄን ያህል በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ተመዝግበው አያዉቁም፡፡ናይጄሪያ ለስድት ሳምንታት ያህል ጥላው የቆየችውን የእንቅስቃሴ እገዳ ያላላችው የበሽታው ስርጭት የመቀነስ አዝማሚያ በማየቱ ነበር፡፡ይሁን እንጂ ተዘግተው የነበሩ የንግድ እና ሌች አገልግሎት ሰጭ ተቋማት እንዲከፈቱ ከመንግስት ትዕዛዝ ከመሰጠቱ በሀገሪቱ ታይቶ የማያውቅ ትልቅ የታማሚዎች ቁጥር መመዝገቡ ናይጄሪያን ውሳኔዋን ሊያቀይራት ይችላል ነው የተባለው፡፡አልጄዚራ እንደዘገበው አዲስ በበሽታው ከተያዙት ሰዎች መካከል 73ቱ የናይጄሪያ የንግድ ማዕከል የሆነችው ሌጎስ ውስጥ የሚኖሩ ናቸው፡፡ምንም እገዳው በተወሰነ መልኩ ሲነሳ ከ20 ሰዎች በላይ በአንድ ቦታ እንዳይሰባሰቡ የሚከለክል ቢሆንም በርካታ ናይጄሪያዊያን የትራንስፖር ጥበቃ መንገድ ላይ በጣም ተጠጋግተው ታይተዋል፡፡ናይጄሪያ ከ2 ሺህ 900 በላይ ሰዎች በቫይረሱ የተያዙባት ሲሆን 98 ናይጄሪያዊያን በኮቪድ 19 ሳቢያ ህይዎታቸው አልፏል፡፡
With Product You Purchase
Subscribe to our mailing list to get the new updates!
Lorem ipsum dolor sit amet, consectetur.
Related Articles
Check Also
Close