AfricaCOVID-19FeaturedHealthNews

የደቡብ ሱዳኑ ተቀዳሚ ምክትል ፐሬዚዳንት ሪክ ማቻር በተደረገላቸው ምርመራ የኮሮናቫይረስ ተገኘባቸው::

የደቡብ ሱዳኑ ተቀዳሚ ምክትል ፐሬዚዳንት ሪክ ማቻር በተደገላቸው ምርመራ የኮሮናቫይረስ ተገኘባቸው::
ሲጂ ቲ ኤን በዘገባው እንዳስነበበው የሀገሪቱ የመከላከያ ሚኒስትር ሆነው በማገልገል ላይ ያሉት የማቻር ባለቤት አንጀሊና ቴኒም በቫይረሱ መጠቃታቸው ታውቋል፡፡የማቻር ፕሬስ ሴክሬተሪ ጀምስ ጋትዴት ዳክ እንዳሉት የቢሮ ሰራተኞቻቸው እና የግል ጠባቂዎቻቸው ጭምር በኮቪድ 19 መያዛቸው ተረጋግጧል፡፡ ምትል ፕሬዚዳንቱ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን በይፋ ለህዝብ መናገራቸውን እና ለቀጣዮቹ 14 ቀናት ከመኖሪያ ቤታቸው ሳይወጡ እንደሚቀመጡም ዳክ አክለው ገልፀዋል፡፡የኮሮና ቫይረስ መከላል ግብረ ሀይልን ምክትል በሊቀመንበርነር የሚመሩት ሪክ ማቻር የተወሰኑት የግብረ ሀይሉ አባላት በቫይረሱ መያዛቸውን ተናግረው የጤና ሚኒስትሩ ግንከቫይረሱ ነፃ ናቸው ብለዋል፡፡በደቡብ ሱዳን የኮሮና ቫይረስ ዘዘግይቶ ቢከሰትም በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር 347 መድረሱ ተሰምቷል፤ ስድስት ሰዎችም በቫይረሱ ሳቢያ ሞተዋል ተብሏል፡፡

Tags
Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami