አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2012 አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ምክንያት በማድረግ በትግራይ ክልል እየተፈፀመ ያለዉ ግፍ እንዲቆም ህጋዊ መፍትሄ እንደሚያስፈልገዉ የትግራይ ብልፅግና ፓርቲ ለአርትስ ቲቪ ገለፀ ፡፡በክልሉ አሁን ድረስ ቀደም ሲል የነበረዉ የአፈናና የእኔ አዉቅልሀለሁ አገዛዝ አሁንም እንደቀጠለ የተናገሩት የፓርቲዉ ከፍተኛ አመራሮችና አባላት በተለይ የትግራይ ህዝብን ከመላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ለመነጠል የሚደረገዉ ጥረት ተቀባይነት እንደሌለዉ ተናግረዋል፡፡በመሆኑም በክልሉ ያሉ አመራሮች ህብረ ብሄራዊ አንድነትዋ የተጠበቀች ሀገር ለመገንባት በሚደረገዉ ጥረት ላይ በማገዝ ል በክልሉም ሆነ በሀገር ደረጃ ሊያግዙ እንደሚገባ ነዉ የትግራይ ብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮችና አባላት ለአርትስ ቲቪ አስተያየታቸዉን የሰጡት ፡፡በተጨማሪም የክልሉ መንግስት ሀገሪቱ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዉስጥ ሆና ምርጫን አካሂዳለዉ የሚለዉ ሀሳብ ተቀባይነት እንደሌለዉና የህዝብን ጤና አለማስቀደም መሆኑን የፓርቲዉ ከፍተኛ አመራር የሆኑት ዶ/ር ሙሉ ነጋ ተግረዋል፡፡በየትኛውም ቦታ የትግራይ ተወላጆች ሀሳባቸዉን በነፃነት የመግለፅ መብት እንዳላቸዉና በየትኛዉም የሀገሪቱ ክፍሎች ተንቀሳቅሶ የመስራት መብት ልንነፈግ አይገባም ሲሉ ዶ/ር ሙሉ ገልፀዋል፡፡
With Product You Purchase
Subscribe to our mailing list to get the new updates!
Lorem ipsum dolor sit amet, consectetur.
Related Articles
Check Also
Close