ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕና ኪም ጆንግ ኡን በግምባር ተገናኝተው ከተወያዩ በኋላ እኛ የኒውክሌር ጣቢያዎቻችንን መዝጋት ስንጀምር አሜሪካ ግን በኛ ላይ የጣለችውን ማእቀብ ከማንሳት ይልቅ ስም ማጥፋት ላይ ተጠምዳልች ብሏል የሰሜን ኮሪያ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር በመግለጫው።
ሲ ኤን ኤን እንደዘገበው የአሜሪካ የደህንነት አማካሪ ጆን ቦልተን ሰሜን ኮሪያ የኒውክሌር ጣቢዎቿን በውላችን መሰረት እየዘጋች ነው የሚል እምነት የለንም ማለታችውን በመከራከሪያነት አንስቷል የውጨ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ ምግለጫ።
በቅርቡ የቀድሞ የአሜሪካ ወታደሮችን ቅሪተ አካል ወደ ሃገራቸው ምድር መመለሳችን ሌላው የውል አክባሪነታችን ምልክት ነው በማለትም ሰሜን ኮሪያ አሜሪካን ቃልሽን ጠብቂ ስትል ወቅሳለች።
አሜሪካ በበኩሏ ሰሜን ኮሪያ ጋር በተነጋገርንው መሰረት ነገሮች በፍጥነት እየተከናወኑ አይደለም የሚል ወቀሳ ስታቀርበ ትሰማለች።