AfricaEconomyEthiopia

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ2010 በጀት አመት ከ89 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ አገኘሁ አለ፡፡

ገቢዉ ካለፈዉ አመት ጋር ሲነጻጸር የ1/4ኛ አድገት ማሳየቱንና፤ የተጣራ 6.8 ቢሊዮን ብር ማትረፉንም ተናግሯል፡፡
ዛሬ አየር መንገዱ የዘንድሮውን አመት እቅድ አፈጻጸም አስመልክቶ ባቀረበዉ ሪፖርት እንደጠቆመዉ በዚህ ዓመት በአፍሪካ ሀገራት የነበረዉን አለመረጋጋት፣የንግድ ጦርነት ፣የነዳጅ ዋጋ መጨመር ችግር የነበረ ሲሆን፤ከአየር መንገዱ አጠቃላይ ወጪ 40 በመቶ የሚሆነዉ ለነዳጅ ወጪ ሆኗል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም እንደተናገሩት በ2010 ካከናወኗቸዉ ስራዎች መካከል የሎጀስቲክስ አገልግሎት መጀመር፣14 አዳዲስ አውሮፕላኖችን መግዛት ፣8 አዳዲስ የበረራ ጣቢያዎችን መክፈት ፣11 ሺህ 92 ቤቶችን ጨርሶ ማስረከብ እና በመስተንገዶ ዘርፍ ባለ 4 ኮከብ አየር መንገድነት ማዕረግ ማግኘትን ናቸው ብለዋል፡፡

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami