የአንድነት ጉባኤው የተካሄደው በኢትዮጲያ ሙስሊሞች ተቋማዊ ለውጥ የጋራ ኮሚቴ አዘጋጅነት ነው፡ሀጂ ዑመር ሰኢድ የኮሚቴው ምክትል ፀሃፊ እንደገለፁት የጉባኤው አብይ አላማ የሀገራችን ሙስሊሞችን አስተባብሮ አንድነቱን ጠብቆ የሚመራ በይዘትም በአደረጃጀትም ጠንካራ እና ሁሉን አቀፍ መሪ ድርጅት የሚቋቋምበት ህግ እና አደረጃጀት የሚያመላክት ምክረ ሀሳብ ማቅረብ እንዲሁም ወደአንድነት መምጣት ነው ብለዋል፡፡ የአንድነት እና ትብብር ኮሚቴው ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት እና ከኢትዮጲያ ሙስሊሞች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ በተወጣጡ 9 አባላት የተዋቀረ ነው፡፡ የመጅሊሱን አደረጃጀት በተመለከተም ኮሚቴው የዝግጅት ስራዎችን ጨርሷል ስምምነቱን እና አንድነቱን ለማብሰርም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ እና የሙስሊሙ ማህበረሰብ በሚገኙበት የጋራ እና አንድነት ስምምነት ማብሰሪያ መድረክ እስከ ህዳር 2011 ባለው ጊዜ ውስጥ እንደሚዘጋጅ ነው በጉባኤው የተገለፀው፡፡