በኮንስትራክሸን ፕሮጀክት ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት በዋና ዳይሬክተርነት እንዲሁም በኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የኮንትራት አስተዳደር እና በምህንድስና ግዢ ላይ በሃላፊነት ሲያገለግሉ ቆይተዋል።
ኃላፊው በቅርቡ የኢትዮጲያ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው የተሾሙትን እና የቀድሞ የተቋሙን ኃላፊ ኢንጂነር ሃብታሙ ተገኝን በመተካት ባለስልጣን መስሪያ ቤቱን ይመራሉ፡፡
የአዲስ አበባከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፅ/ቤት እንዳስታወቀው የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን በአጭር ጊዜ ማጠናቀቅ እና በከተማዋ የመንገድ መሰረተ ልማት ላይ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችሉ አዳዲስ ፕሮጀክቶችን መቅረጽ በቀዳሚነት ኃላፊው የሚያከናውኗቸው ተግባራት መሆናቸውንም ተገልጿል።
ኢ ቢ ሲ እንደዘገበው