AfricaEthiopiaPolitics

የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ከጅቡቲ ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌ ጋር በጅቡቲ ተወያዩ።

የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በድረ ገጹ እንዳስታወቀዉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ፥ በኢትዮጵያ እና ጅቡቲ መካከል ያለው ግንኙነት በሁኔታዎችና በአጋጣሚ የማይለወጥ ስትራቴጂካዊ ወዳጅነት ነዉ ብለዋል፡፡
ዶክተር ወርቅነህ፥ በድሬዳዋ በተፈጠረው ክስተት የጅቡቲ ዜጎች ህይወታቸውን በማጣታቸው ማዘናቸውን ገልጸዋል፡፡
የተፈጠረው ክስተት የሁለቱን ህዝቦች አጠቃላይ ግንኙነት አያሳይም ያሉት ዶክተር ወርቅነህ፥ ጥፋተኞቹ በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገ በመሆኑ በሕግ ተገቢውን እርምጃ እንደሚያገኙ ተናግረዋል።
በጅቡቲ የሚኖሩ የተወሰኑ ኢትዮጵውያን በፀጥታ ስጋት ምክንያት ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን ጠቅሰው ኢትዮጵያዊያን ጅቡቲን ሁለተኛ ሀገራቸው አድርገው የሚቆጥሩ በመሆኑ በሀገሪቱ ያለስጋት መኖር እንዲችሉ የጅቡቲ መንግስት አስፈላጊውን ሁሉ እንዲያደርግ ዶክተር ወርቅነህ ጠይቀዋል፡፡
የጅቡቲ ፕሬዝዳንት ኢስማኢል ኦማር ጊሌ በበኩላቸው፥ ኢትዮጵያዊያን በጅቡቲ ውስጥ ያለ ምንም ችግር መኖር እንደሚችሉና መንግስታቸውም ይህን ለማድረግ እንደሚሰራ አረጋግጠዋል፡፡

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami