Uncategorized

ማርክ ዙከርበርክ ለእግር ኳስ አፍቃሪዎቸ አዲስ የምስራች ይዞ ብቅ ብሏል፡፡

እስካሁን በዓለም ላይ ብዙ ተመልካች ያለውና በብዙዎች ዘንድ ተወዳጅ የሆነውን እግር ኳስን በቀጥታ መከታተል የሚቻለው በቴሌቭዥን ቻናሎች አልያም በዌብ ሳይቶች ነበር፡፡
አሁን ደግሞ ፌስ ቡክ የራሱን መተግበሪያ ተጠቅሞ የስፔን ላሊጋ ጨዋታዎችን ለደንበኞቹ ለማሳየት ተዘጋጅቷል የሚል ወሬ ተሰምቷል፡፡
ዘ ጋርዲያን እንደዘገበው የፌስ ቡክ ተጠቃሚዎች ከእንግዲህ በቀላሉ መተግበሪያውን ተጠቅመው የስፔን ላሊጋ ጨዋታዎችን በቀጥታ መከታተል ይችላሉ፡፡
ህንድን ጨምሮ ስምንት የሚሆኑ ሀገሮች የዕድሉ ተጠቃሚዎች እንደሆኑም ዘገባው አመላክቷል፡፡
ፌስ ቡክ ባደረገው ስምምነት ህንድ፣ ባንግላዲሽ፣ ኔፓል፣አፍጋኒስታን፣ ማልዲቭስ፣ ብሁታን ስሪላንካና ፓኪስታን ውስጥ ነው አገልግሎቱን የሚሰጠው፡፡
በነዚህ ሀገሮች በጠቅላላው 348 ሚሊየን የፌስቡክ ተጠቃሚዎች መኖራቸውን ከግምት በማስገባት ነው ፌስ ቡክ ወደ ስራው የገባው፡፡

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami