ቪኦኤ እንደዘገበዉ ሌሎች የተለያዩ የውጭ ሀገር የገንዘብ ኖቶችን ጨምሮ ከ92 ሺህ በላይ የአሜሪካን ዶላር ነዉ የተያዘዉ።
በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 92 ሺህ 100 የአሜሪካ ዶላር፣ 13 ሺህ ዩሮ፣ 17 ሺህ የአረብ ኢሚሬት ድርሃም እና 52 ሺህ 600 የኢትዮጵያ ብር በቁጥጥር ስር መዋሉን የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉሙሩክ ባለስልጣን የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ኤፍሬም መኮንን ገልጸዋል።
የገንዘብ ኖቶቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት ከነሃሴ 1 እስከ 7 ቀን 2010 በተደረገ ዘመቻ ነው፡፡