አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 28 ፣ 2012 የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ያጋራ መኖራያቤቶች የፀረ ተህዋስ ርጭት ተደረገ ::በብርጭቆ ኮንዶሚኒያም ነዋሪ የሆኑት ኢንጀነር ሙኩሪያ በየነ የተባሉ ግለሰብ በተለምዶ ብርጭቆ ኮንዶሚኒየም ተብሎ በሚጠራው የጋራ መኖርያቤቶች ሳይት የፀረ ተህዋስ ርጭት አካሄደዋል፡፡
የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ህብረተሰቡ ከመንግስት ጎን በመሆን የሚችለውን ጥረት ማድረግ እንዳለበት የገለፁት ኢንጀነር መኩሪያ በራሳቸው ወጪ 10ሺ ነዋሪዎች የሚኖሩበትን ያጋራ መኖርያቤቶች የእግረኛ መመላለሻዋች ፤ የመኪና ማቆሚያዎችና መወጣጫዎች ላይ የፀረ ተህዋስ ርጭት አድርገዎል፡፡
የፀረ ተህዋስ ርጭት ስራውን ለመስራት 18 ሺ ሊትር ውሃ እና 270 ሊትር ኬሚካል የተጠቀሙ ሲሆን የፀረ ተህዋስ አቀማመም ሂደቱን በተመለከተ ከድንገተኛ እሳትና አደጋ ኤጀንሲ ጋር በመነጋገር መዘጋጀቱን በመግለፅ ለዚህ ስራ የሚሆን ዘጠኝ ሺ 6 መቶ ብር ወጪ ማድረጋቸውን ነው የተናገሩት፡፡የኮሮናን ቫይረስ ለመከላከል ህብረተሰቡ ሳይዘናጋ በተለይም ከጤና ሚኒስቴር እና ከህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሚተላለፉ መረጃዎችን በመተግበር እንዲሁም ደግሞ ከመንግስት ጎን በመሆን ለችግሩ መረባረብ እንደሚገባ ነው ያሳሰቡት፡፡