COVID-19EthiopiaFeaturedHealthNews

የጤና ሚኒስቴር የቴንሴንት ፋውንዴሽን የላካቸውን የኮሮና ቫይረስ መመርመሪያ ቁሳቁሶች ተረከበ::

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣2012 

ጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ እነዳስታወቁት  የቴንሴንት በጎ አድራጎት ድርጅት ኮቪድ19 ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚሰራውን ስራ ለማገዝ የሚያስችሉ 1ነጥብ6 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጡ የመመርመሪያ ኪቶችንና ጓንቶችን ድጋፍአድርጓል፡፡

ዶ/ር ሊያ በጎ አድራጎት ድርጅቱ  ስላደረገልን ድጋፍ ልባዊ ምስጋናዬን እየገለጽኩ ሁሌም ትብብራቸው የማይለየንን በኢትዮጵያ የቻይና ኤምባሲ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድን ላመሰግንን እወዳለሁ ብለዋል  በፌስቡክ ገጻቸዉ፡፡

የቴንሴንት ኩባንያ የታዋቂው ማኅበራዊ ትስስር ገጽ “ዊ ቻት” ባለቤት ሲሆን በዋናነትበቴክኖሎጂ ዘርፍ  የተሰማራ ኩባንያ ነው። የኩባንያው ፋውንዴሽን ለኢትዮጵያ 100 ሺህ የመመርመሪያ መሳሪያዎችና ሁለት ሚሊዮን የህክምና ጓንቶችን የላከ ሲሆን፤ ድጋፉን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ቦሌ ዓለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው ተረክበዋል።

በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ታን ጄን በዚሁ ጊዜ ሀገራቸው የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን የመከላከሉ ስራ በተናጥል ሳይሆን በትብብርና በጋራ እንዲከናወን እንደምትሻ ገልጸዋል።

ኢትዮጵያና ቻይና ግንኙነታቸውን ቀደም ብለው ወደ ሁሉን አቀፍ ስትራቴጂክ አጋርነት ማሳደጋቸውን አስታውሰው፤ ድጋፍም ይህንኑ እንደሚያሳይ ተናግረዋል።ቻይናን ጨምሮ ኮሮናን በስኬት መከላከል ከቻሉ አገራት ጀርባ ያለው ምስጢር የምርመራ ተደራሽነት መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

Tags
Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami